
ስለ እኛ
በቪዛ መረጃ እና በቋንቋ መሃል ሁል ጊዜም የተወሰነ ክፍተት አለ ። ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ትልልቅ የኤጀንሲ ተቋማትም ይሄንን ክፍተት ለራሳቸው ግላዊ ጥቅም ሲያውሉት አይተናል። እኛ የቪዛ አንድ ሁለት ቡድኖች የቪዛ መረጃን ለሁሉም ሰው በአማረኛ ቀለል አድርገን ማቅረብን ዋና አላማችን አድርገን ተነስተናል። መረጃዎችን አቅርበንሎታል የእርስዎ ስራ የተለያዩ ኤምባሲዎች፣ የትምህርት ተቋማት እንዲሁም የውጪ ሃገር ስራ ቀጣሪዎች ጋር ማመልከት ብቻ ነው።
ፈረስ ያደርሳል እንጂ አይዋጋም እንዲሉ፣ የፕሪምየም አገልግሎታችን እርስዎ በራስዎ ዌብሳይታችን ላይ ገብተው የሚፈልጉትን መረጃ ወስደው ማመልከት እንዲችሉ በጥንቃቄ ተነድፎ ተሰርቷል። ቡድናችን ሁሌም አዳዲስ መረጃዎችን ከኤምባሲዎች፣ ከትምህርት ተቋማት እንዲሁም ከተለያስዩ የውጪ ሃገር ስራ ቀጣሪዎች ሰብስበን "አፕዴት" እናረግዎታለን።
በቪዛ መረጃ እና በቋንቋ መሃል ሁል ጊዜም የተወሰነ ክፍተት አለ ። ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ትልልቅ የኤጀንሲ ተቋማትም ይሄንን ክፍተት ለራሳቸው ግላዊ ጥቅም ሲያውሉት አይተናል። እኛ የቪዛ አንድ ሁለት ቡድኖች የቪዛ መረጃን ለሁሉም ሰው በአማረኛ ቀለል አድርገን ማቅረብን ዋና አላማችን አድርገን ተነስተናል። መረጃዎችን አቅር በንሎታል የእርስዎ ስራ የተለያዩ ኤምባሲዎች፣ የትምህርት ተቋማት እንዲሁም የውጪ ሃገር ስራ ቀጣሪዎች ጋር ማመልከት ብቻ ነው። ፈረስ ያደርሳል እንጂ አይዋጋም እንዲሉ፣ የፕሪምየም አገልግሎታችን እርስዎ በራስዎ ዌብሳይታችን ላይ ገብተው የሚፈልጉትን መረጃ ወስደው ማመልከት እንዲችሉ በጥንቃቄ ተነድፎ ተሰርቷል። ቡድናችን ሁሌም አዳዲስ መረጃዎችን ከኤምባሲዎች፣ ከትምህርት ተቋማት እንዲሁም ከተለያስዩ የውጪ ሃገር ስራ ቀጣሪዎች ሰብስበን "አፕዴት" እናረግዎታለን።
የቪዛ አንድ ሁለት መስራች ጉዞ
ከኢትዮጲያ- ፓላንድ - ከፓላንድ ወደ ካናዳ

ብሩክ ብርሃኑ (የቪዛ አንድሁለት መስራች)

ፖላንድ
እንደማንኛውም የዩኒቨርሲቲ ተመራቂ የአምስት አመት የዩኒቨርሲቲ ትምህርቴን ካጠናቀቅኩኝ በኋላ የውጪዎችን ትምህርት ለመቅመስ እና ራሴን ለማሸነፍ ወደ ፓላንድ በትምህርት ለመሄድ ዶክመንቶቼን ማሰባሰብ ጀመርኩኝ። ውጣ ውረዱ፣ ከዩኒቨርሲቲ ኮስት ሼሪንግ ክፍያ ጀምሮ እስከ ፓስፖርት ማሳደስ ድረስ። ከተለያየ ሰዎች የምሰማው የተዛባ መረጃ ብዛት፤ ይሄ ሁሉ እያለ ግን ውስጤ ይሳካል የሚለኝ ድምጽ አለ። በመጨረሻም ያለምንም ኤጀንት ራሴ ከትምህርት ቤት ክፍያ ጀምሮ እስከ ኤምባሲ ድረስ ያለውን ውጣ ውረድ አሸንፌ ከኢትዮጵያ ወደ ፓላንድ ሄድኩኝ።


ብሩክ ብርሃኑ (የቪዛ አንድሁለት መስራች)

ካናዳ

ለት ወራት ፓላንድ ከቆየው በኋላ ከባችለር ዲግሪዬ ጋር የሚሄድ የትምህርት እድል መፈለግ ጀመርኩኝ። የብዙ ሃገራትን የቪዛ መስፈርት ለማሟላት ሪሰርች ማድረግ ጀመርኩኝ፣ አውስትራሊያ፣ ኖርዌይ፣ ጀርመኒ፣ ኢንግላንድ፣ ፈረንሳይ እና ካናዳ። ቀላል አልነበረም መረጃ ማሰባሰቡ በተለይም የኢትዮጵያ ፓስፖርት ኖሮን ከአንድ ሃገር ወደ ሌላ ሃገር ለማመልከት መሞከር በጣም ከባድ ነበር። እንደ ቪዛ አንድ ሁለት ያለ ዊባስይት ቢኖር እንዴት ስራዬን ሊያቀልልኝ እንደሚችል ሁሌም አስባለው። ከዛም ከሶስት ወር ቆይታ በኋላ ካናዳን መረጥኩኝ። ሁሉንም ዶክመንቶቼን አሰባስቤ አመለከትኩኝ። ከአንድ ወር በኋላ፣ ተሳካ! አስታውሳለው ጂም ውስጥ ነበርኩኝ ከኤምባሲ የተላከልኝን ኢሜል ሳይ፣ ማመን ነበር ያቃተኝ ። በመጨረሻም ከፓላንድ ስድስት ወራት ቆይታ በኋላ ወደ ካናዳ ለመሄድ ሻንጣዬን አዘጋጀው።

ትንሿ ቡድናችን
እኛ ጋር ሲመጡ በግልጽ እና ታማኝ በሆነ መንገድ የሰራነው AI ትክክለኛ እና ወቅቱን የጠበቀ መረጃ ይሰጥዎታል። ቡድናችን በዓለም የተለያዩ አገሮች ቱሪስት ቪዛ (Tourist visa) ፣ የሥራ ቪዛ (Work Visa)፣ የቤተሰብ ቀላቀል እና ሌሎችም ቪዛዎች ላይ የተለያዩ መረጃዎች በመስጠት የተረጋገጠ ውጤት በማምጣት በብዙ ተሞክሮ አስመስክረናል። በመጀመርያው ፌዝ ላይ የትምህርት ቪዛ መረጃን ቀዳሚ ትኩረታችን አድርገን እየሰራን ነው ያለነው!

ብሩክ ብርሃኑ
የቪዛ አንድሁ ለት መስራች እና ዳይሬክተር

ሜቲ ግርማ
የቪዛ አንድሁለት መስራች እና ዲጂታል ማርኬተር

ሚኪያስ ታደሰ
ፕሮዳክት ዲዛይነር / አሲስታንት

እኛን ለማግኝት
የቪዛ መረጃ አገልግሎቶችን በተሟላ መልኩ ዛሬውኑ ያግኙ። ቪዛ አንድ ሁለት የቪዛ ሂደቶች ላይ የሚያስፈልጉዎትን መረጃ በፍጥነት እና በታማኝነት ለመስጠት ዝግጁ ነው።


